Our company, Tana Drilling and Industries Plc is proud to announce that we are managed to produce and supply OD 355mm high-quality HDPE pipes (as per ISO 4427, with PE 100 raw material) for our esteemed customer “BIGETA CONSTRUCTION & BUSINESS PLC” for Water Supply project of DARCHA Woreda Gurage zone which is being financed by Necati Erill and Coordinated.
Project: DARCHA Woreda Water Project (The objective of the Project is to improve access to safe water by expanding and improving water supply facilities through the development of deep wells, expansion of distribution networks, construction of distribution reservoirs in Gurage zone Darcha Woreda)
The project would underpin economic development in woreda and improve the lives and health of the population by delivering reliable, safe and affordable water supply and it is key for the success of other commercial and economic reforms in the region.
Project relevance: The project is relevant as it contributes toward meeting the demand for water supply by the communities in Darcha Woreda and the surrounding towns and eases the daily burden of the population in the area.
Location: Gurage zone Darcha Woreda
Beneficiaries: more than 7,500 households (population) of Gurage zone Darcha Woreda, SNNP
Implemented by: Give water and SNNP
Client: BIGETA CONSTRUCTION & BUSINESS PLC
At Tana Drilling and Industries Plc, we are always striving for high quality, prompt delivery, and competitive rates… and these are the reasons why we are having wide acceptance and an overwhelming market reputation in Ethiopia.
Please visit our website www.tdiplc.com to know more about our products and services and inquiry.
Tana Drilling and Industries plc
‘Committing to Quality, Committing to You!”
በዓለማችን በርካታ አገሮች በኢኮኖሚ እድገታቸው ከፍተኛ ደረጃ የደረሱት የውሃ ሀብታቸውን በማልማት ከዚያ የሚገኘውን ገቢ ለሌሎች ሴክተሮች በማዋል ነው። በተለያዩ የታሪክ ምዕራፎች ዘመን ፈጣን ዕድገት ያስመዘገቡ ሀገሮች ውሃን ከመሰለ የተፈጥሮ ሀብት ጋር ያላቸው ትስስር ከፍተኛ ነው። በእርግጥ ለማይነጥፍና ዘላቂ እድገት የሰው ሃብት በተለይም ጉልበትና እውቀት ወሳኝ ጉዳዮች ቢሆኑም ያለንን እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ለላቀ ጥቅም ማዋል የአድገት መሠረት መሆኑን በጽናትም በተግባርም ተረጋግጧል። ሀገራችን ከፍተኛ የከርሰ ምድርና ገፀ ምድር ውሃ ከምችት ያለባት ብትሆንም ከሀብቱ በመጠቀም ረገድ ስሟ ጐልቶ ሳይጠቀስ ቆይቷል። ኢትዮጵያ ያሏትን የተፈጥሮ ሃብቶች ከግምት ውስጥ ያስገባ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ተነድፈው ወደ ተግባር ከገባች ወዲህ ለውጥ ከተመዘገበባቸው ዘርፎች እንዱ የውሃ ሃብት አጠቃቍማችን ሆኗል።
ለዚህ ደግሞ በአገር አቀፍና በከልሎች ከተቋቋሙት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች በተጨማሪ በግል ባለሀብቱ የተቋቋሙ የቁፋሮ ድርጅቶችና የውሃ ግንባታ ሥራዎች ግብዓት አቅራቢዎች የውሃ ኘሮጀክቶቹ በፍጥነት እንዲከናወኑ የበኩላቸውን ድርሻ የተወጡ ድርጅቶች ድርሻ በዋናነት ይጠቀሳል። ከነዚህም መካከል በተለይ በመላው ኣገሪቱ በሚያመርታቸው የኘላስቲክ ቧንቧዎችና የቁፋሮ ሥራዎች ተደሽ የሆውን ጣና ቁፋሮና ኢንዱስትሪ በግንባር ቀደምትነት መርጠነዋል።
የድርጅቱ መሥራች፣ ባለቤትና ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ እፀገነት በርሄ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እንዳጠናቀቁ ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ (እርሻ ምህንድስና ተመርቀዋል፣ ከዚያም በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመምሀርነት አገልግለዋል፤ ወደ እንግሊዝ እገርም እድል አግኝተው በመሄድ በመሰኖ ምህንድስናና በከርሰ ምድር ምህንድስና ሁለት ማስተሮችን አግኝተዋል፤ ከዚያም በተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) 10 ዓመታት ያህል ኢትዮጵያ ውስጥም ከኢትዮጵያ ውጪም ሰርተዋል። በ UNICEF ከሚመሩት ስፋ ያለ ኘሮግራም ውስ ውሃ ትልቁን ድርሻ የያዘ ነበር። በርካታ የቁፋሮም ሆነ የውሃ ሥራዎችን ከሙያ አኳያ ችግሩ በከፋባቸው እንደዚሁም በጦርነት በወደሙ ቦታዎች ሳይቀር ተሠርተው በአለም አቀፍ ደረጃ ሠርተዋል። በመጨረሻም የ UNICEF ቆይታቸውን በመተው ወደ ሀገራቸው ተመልሰው በቀሰሙት እውቀትና ባካበቱት ልምድ በኢትዮጵያ የንፁህ ውሃ መጠጥ ችግርን ለማቃለል ቡሚደረገው ጥረት ውስጥ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ለማበርከት በግላቸው ጣና ጉድጓድ ቁፋሮ ድርጅትን አቋቱመው ሥራ ለጀመር እንደቻሉ ከዳጉ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
የጥልቅ ጉድጓድ የውሃ ቁፋሮ ሥራ በጣም ሪሰክ ያለበት የሥራ ዘርፍ በመሆኑ ብዙ ጊዜ በሙንግሥት ደረጃ ሊሠሩ የሚችሉ ናቸው የሚሉት አቶ እፀገነት ይሁንና ትኩረት ስጥተህ ቅን ሆነህ ሥራህን አከብረህ በትጋት ቀን ከሌሊት ከተረባረብክ ያሉትን ሪስኮች ሁሉ ተቋቁመህ መወጣት ትችላለህ ሲሉ የሥራውን ፈታኝ ሁኔታ አብራርተዋል። በዚህ ሁኔታ እሳቸው ወደሥራው እራሳቸውን አዘጋጅተው በመግባት እስሁን በመላ አገሪቱ ከ500 ያላነሱ የጥልቅ ጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ሥራዎችንና ተያያዥ ሥራዎችን ውጤታ በሆነ መልኩ ለማከናወን ችለዋል።
በ1997 ዓ.ም የጀመሩትን የቁፋሮ ሥራ በሀገራችን ከስርቪስ ወደ ማኑፋክቸሪንግ በደረገው ሽግግር የበኩላቸውን ሀገራዊ አስተዋጽኦ ለማበርከት ከ4 ዓመት በፊት ጀምሮ ጐን ለጐን አለም አቀፍ ታዋቂነት ካላቸው እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የቱቦ ማምሪቻ ማሽኖችን በማስገባት የውሃና ፍሳሽ ቱቦ የማምረት ሥራም ለአገልግሎት ማብቃታቸውንም ለዳጉ ተናግረዋል።
ጣና ቱፋሮና ኢንዱስትሪ በማምረቻው ዘርፍ በአሁኑ ሰዓት ወደ 38 ሺ ትሪክ ቶን የኘላስቲክ ቧንቧዎችን (HDPE and UPVC) የማምረት አቅም ያለው ነው፤ አለም አቀፍ የእውቅና ሠርተፊኬት ISO 9001/2015 ያሟላ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል።
ኩባንያው ሁልጊዜም ለአዳዲስ ሃሳቦችና እድገት ከፍታ የሚተጋ በዘመናዊነት ፈጠራ እና የቴክኖሎዲ ሽግግር ቀድሞ የሚገኝ እንደሆነም ነው አቶ እፀገነት የነገሩን። የሚያመርታቸው የኘላስቲክ ቱቦዎች በኢትዮጵያና አካባቢው የአየር ፀባይ ጋር ተስማሚ እንደሆነም ሳይጠቅሱ አላለፉም።
በአጠቃላይ ጣና ቁፋሮና ኢንዱስትሪ ኩባንያ በየጊዜው ለደንበኞቹ እርካታ ትኩረት በመስጠት በከፍተኛ ጥረትና እድገት ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የበኩሉን ለመወጣት ቁርጠኛ መሆኑንም አቶ እፀገነት አያይዘው ገልፀዋል።
በሀገራችን የውሃው ዘርፍ ላይ የኘሮጀክቶች አፈጻጸም ሆነ ሀብቱን በተሻለ መልኩ ለሠጠቀም እንደ ጣና ቁፋሮና ኢንዱስትሪ አይነት ድርጅቶች ገንቢ ሚና ያላቸው በመሆኑ ሊበረታቱ ይገባል እንላለን።
ለአሁኑ አጠቃላይ የጣና ቁፋሮና ኢንዱስትሪ ገጽታን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።
የድርጅቱን ገጽታ በከፊል
ጣና ቁፋሮ እና ኢንዱስትሪ የግል ኩባንያ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለገጠሩና ለከተማ ሕብረተሰብ የውሃ ሽፋን ለማዳረስና ለማሳደግ የሚተጋ ነው።
ዋና ዓላማውም ተመጣጣኝ ዋጋ እና ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምርቶች በተቀላጠፈ ሁኔታና በአጭር ጊዜ ለማምረት ሲሆን፤ ይህንን ለማሳካት ከጀርመንና ከጣልያን የማምረቻ መሣሪያዎችን በማስገባት የኘላስቲክ ቱቦ ምርቶች ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ግብአቶች ያመርታል።
ጣና ቁፋሮና ኢንዱስትሪ ለዘመናዊ የማምረቻ ቴክኖሎጂውና ከፍተኛ ጥራት ባላቸው ንፁህ ጥሬ እቃዎች የተለያዩ መጠን ያላቸውን የኘላስቲክ ቧንቧዎች (HDPE and UPVC) በማምረት ለንፁህ መጠጥ ውሃ ዝርጋታ፣ ለፍሳሽ ማስወገጃ፣ ለሜካናይዝድ እርሻ ለመሳሰሉት አገልግሎቶች እንዲውሉ በማድረግ ለሀገራችን እድገት ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል።
በተለይ HDPE እና UPVC ቱቦ የውሃ ማከፋፈያ መስመር ዝርጋታ ፣ ለውሃ ማውረጃና ቆሻሻን ማስወገጃ ዘዴዎች፣ ኬሚካል፣ ጋዝና የውሃ ማስተላለፊያ፣ ቆሻሻ የሚተላለፍበት ቱቦ እና የውሃ ማጣራት ዘዴ ለግብርና መስኖ፣ ለመብራት እና ለቴሌኮሙኒኬሽን ማከፋፈያ ተስማሚ ናቸው።
ጣና ቁፋሮና ኢንዱስትሪ ያነገበውን ራዕይ እውን ለማድረግ እያመረታቸው ከሚገኙት የኘላስቲክ ቧንቧዎች በተጨማሪ የኘላስቲክ ቧንቧዎች መገጣጠሚያዎችን (HDPE Fittings) በማምረትና ለገበያ በማቅረብ የደንበኞችን ችግር ከመቅረፍ አልፎ የውጭ ምንዛሬ ብክነትን ለመታደግ ችሏል። እነዚህን መገጣጠሚያዎች ሀገር ውስጥ በማምረታችን ምክንያት የደንበኞቻችንን እርካታ ለማሳደግ ችለናል።
የጣና ቁፋሮና ኢንዱስትሪ በአለም አቀፍ የእውቅና ሠርተፊኬት ISO9001/2015 ያለው ድርጅት ነው።